ዜናዊ መግለጫ

ሊትልተን፣ ኮሎራዶ፣ ጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም.
 

በዓማርኛ በነፃ መክተቢያ የግዕዝኤዲት ገጽ
 

ኣብሻ/ኢኮሶ ኩባንያ በዛሬው ቀን ኣዲስ የግዕዝ ፕሮግራም ኣቅርቧል። ይህም ግዕዝኤዲት ገጽ በዓማርኛ በነፃ የሚያስከትብ ኤችቲቲፒ://ፍሪታይፒንግ.ግዕዝኤዲት.ኮም ወይም http://freetyping.geezedit.com በሚባል ኣዲስ ድረገጽ ይገኛል።
 
ኣብሻ በ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. በዶ/ር ኣበራ ሞላ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሠናይት ከተማ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ይህ የኮሎራዶ ተቋም ግዕዝን በኮምፕዩተር መጠቀም እንዲቻል መፍጠሩንና ሞዴት የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያን በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ለዶስ ኮምፕዩተር ማቅረቡ ይታወሳል። ግዕዝን በኮምፕዩተር መክተብ በዶ/ር ኣበራ ከመጀመሩ በፊት ፊደሉ የሚጻፈው በእጅ ወይም ማተሚያ ቤቶች ብቻ ነበር። የኣብሻ ዘዴ በመባል በታወቀው
በኣሁኑ ኣዲ ፈጠራ ብዛታቸው ከ፭፻፷፫ በላይ የሆኑት የግዕዝ ፊደላት እያንዳንዳቸው የሚከተቡት እንደ እንግሊዝኛው ኣጻጻፍ ዓይነት ኣንድ ወይም ሁለት መርገጫዎች ብቻ በመጠቀም ነው። ስለዚህ በእዚህ ኣዲስ ቀላል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ጊዜና ገንዘብ እናትርፍ።
 
ግዕዝ በኢትዮጵያ ለብዙ ሺህ ዘመናት ስንጠቀምበት የቆየ ፊደል ሲሆን በኣሁኑ ጊዜ ከሚገለገሉበት ቋንቋዎች መካከል ምኢን፣ ቢለን፣ ቤንች፣ ትግረ፣ ትግርኛ፣ ኣገው፣ ኦሮሚፋ፣ ዓማርኛ፣ ጉራጌና ግዕዝ ይገኙበታል። ከእዚህ ሌላ ተጠቃሚ ቋንቋዎች ስለጨመሩ ኣዳዲስ ፊደላት መፍጠርም ቀጥሏል።
 
ድረገጽ ላይ በነፃ የግዕዝኤዲት ገጽ ለመጠቀም በጣም ቀላል ሊሆን የቻለው እያንዳንዱን ፊደል ከሁለት መርገጫዎች ባልበለጡ የሚያስከትብ የባለቤትነት መብቱ (ፓተንት / Patent) ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለበት በኣዲስ ቴክኖሎጂ ላይ ስለተመረኰዘ ነው። ከድረገጽ ማንበብ የሚችል ማንም ተጠቃሚ በነፃ ከከተበ በኋላ ጽሑፉን ማረም፣ ማስቀመጥ፣ ማተምና ድረገጽም መሥራት የሚያስችል ውድና ኣዲስ ስጦታ ነው። ይህ ኣዲስ ግኝት ባይኖር የግዕዝ ተጠቃሚዎች ኣንዳንዶቹን ፊደላት ወይም ቅርጾች የሚከትቡት ከሦሶት እስ
ስድስት መርገጫዎች በመጠቀምና ዋየሎች ላይ ያሉትንና ኣንዳንዶቹንም ለመድገም ባዶ ስፍራን መጨመር ኣስፈላጊም ነበር። ኣሁን ግን ማንኛውንም የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝ፣ ምልክትና ማዜሚያ ለመክተብ ከሁለት መርገጫዎች በላይ መጠቀም ኣያስፈልግም።
 
ለተጨማሪ መረጃ ግዕዝኤዲት.ኮም ወይም ኢትዮፒክ.ኮም ድረገጾች መጎብኘትና ኢ-ሜይልም ለኢትዮጵያዊው@ኤኦኤል.ኮም ወይም ግዕዝኤዲት@ኤኦኤል.ኮም መላክ ይቻላል። ኣድራሻው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር Ethiopian Computers & Software, 9781 W. Fremont Pl., Littleton, CO 80128, USA ኣሜሪካ ሲሆን የስልክ ቍጥሩ 1-303-972-2186 ነው።
 

ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ጀምሮ ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠረ!