ዜናዊ መግለጫ

ብራይተን፣ ኮሎራዶ፣ ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም.
 

ነፃው ግዕዝኤዲት ገጽ በጉግል ዓማርኛ መፈለጊያ
 

ኣብሻ/ኢኮሶ ኩባንያ በዛሬው ቀን ኣዲስ የጉግል መፈለጊያ የግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ ኣቅርቧል። ይህም ግዕዝኤዲት ገጽ በዓማርኛ በነፃ የሚያስከትብ ኤችቲቲፒ://ፍሪታይፒንግ.ግዕዝኤዲት.ኮም ወይም http://freetyping.geezedit.com በሚባል ድረገጽ ውስጥ ይገኛል።
 
ኣብሻ በ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. በዶ/ር ኣበራ ሞላ እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሠናይት ከተማ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ይህ የኮሎራዶ ተቋም ግዕዝን በኮምፕዩተር መጠቀም እንዲቻል መፍጠሩንና ሞዴት የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያን በ፲፱፻፹ ዓ.ም. ለዶስ ኮምፕዩተር ማቅረቡ ይታወሳል። ግዕዝን በኮምፕዩተር መክተብ በዶ/ር ኣበራ ከመጀመሩ በፊት ፊደሉ የሚጻፈው በእጅ ወይም ማተሚያ ቤቶች ብቻ ነበር። የኣብሻ ዘዴ በመባል በታወቀው
በኣሁኑ ኣዲ ፈጠራ ብዛታቸው ከ፭፻፷፫ በላይ የሆኑት የግዕዝ ፊደላት እያንዳንዳቸው የሚከተቡት እንደ እንግሊዝኛው ኣጻጻፍ ዓይነት ኣንድ ወይም ሁለት መርገጫዎች ብቻ በመጠቀም ነው።

ይኸንኑ መክተቢያ ሕዝቡ በነፃ እንዲጠቀምበት ኩባንያው ባላፈው ጥቅምት ድረገጹን በነፃ ማቅረቡ ይታወሳል። ድረገጽ ላይ በነፃ የግዕዝኤዲት ገጽ ለመጠቀም በጣም ቀላል ሊሆን የቻለው እያንዳንዱን ፊደል ከሁለት መርገጫዎች ባልበለጡ የሚያስከትብ የባለቤትነት መብቱ (ፓተንት / Patent) ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለበት በኣዲስ ቴክኖሎጂ ላይ ስለተመረኰዘ ነው። ከድረገጽ ማንበብ የሚችል ማንም ተጠቃሚ በነፃ ከከተበ በኋላ ጽሑፉን ማረም፣ ማስቀመጥ፣ ማተምና ድረገጽም መሥራት የሚያስችል ውድና ኣዲስ ስጦታ ነው። ይህ ኣዲስ ግኝት ባይኖር የግዕዝ ተጠቃሚዎች ኣንዳንዶቹን ፊደላት ወይም ቅርጾች የሚከትቡት ከሦሶት እስ ስድስት መርገጫዎች በመጠቀምና ዋየሎች ላይ ያሉትንና ኣንዳንዶቹንም ለመድገም ባዶ ስፍራን መጨመር ኣስፈላጊም ነበር። ኣሁን ግን ማንኛውንም የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝ፣ ምልክትና ማዜሚያ ለመክተብ ከሁለት መርገጫዎች በላይ መጠቀም እንዳላስፈለገ ይታወሳል።

በሚሸጠው ግዕዝኤዲት በግዕዝ መፈለግ ኣስቸጋሪ ኣይደለም። ነፃው የግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ ግን በኣዲሱ የጉግል መፈለጊያ ለመጠቀም “Search” የሚለውን በመጫን የጉግል መፈለጊያ ሳጥን ይወጣል። መስመሩ ውስጥ በተለመደው የግዕዝኤዲት ኣከታተብ መጠቀም ዓማርኛውን ያስከትባል። ከእዚያም ከቀኝ የሚገኘውን “Search” መጫን ጉግል የሚያውቃቸውን የዓማርኛ ጽሑፎች ዝርዝር ያስቀርባል። የሚፈለገውን መርጦ መጫን ጽሑፉን ይከፍታል። በጉግል ግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ በእንግሊዝኛ ለመፈለግ “Alphabet/ፊደል” ከእዚያም “Latin/እንግሊዝኛ” የሚለውን መርጦ መጫን የሚፈለገውን ቃል ወይም ቃላት ሳጥኑ ውስጥ በእንግሊዝኛ የማስከተብና መፈለግ ምርጫ ይሰጣል። 

ለተጨማሪ መረጃ ግዕዝኤዲት.ኮም ወይም ኢትዮፒክ.ኮም ድረገጾች መጎብኘትና ኢ-ሜይልም ለኢትዮጵያዊው@ኤኦኤል.ኮም ወይም ግዕዝኤዲት@ኤኦኤል.ኮም መላክ ይቻላል። ኣድራሻው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር Ethiopian Computers & Software, 10145 E. 143 Way, Brighton, CO 80602, USA ኣሜሪካ ሲሆን የስልክ ቍጥሩ 1-303-835-8025 ነው።
 

ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ጀምሮ ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠረ!
 



 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ኢ-ሜይል | Ethiopian@aol.com | Top ወደላይ

 © ABSHA/ECS 1985-2009 (መብት) የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር፣ ፲፱፻፸፯-፳፻፪ ዓ.ም.