ዓማርኛ
(Amharic)
The Amharic Typewriter Font
(Fake Amharic)
የዓማርኛ የጽሕፈት
መኪና ቅጥልጥል ፊደል

የብዙ
ሺህ ዕድሜ ያለው የግዕዝ ወይም ኢትዮፒክ ፊደል እንደ ላቲኑ እያንዳንዱ ፊደል እራሱን የቻለ እንጂ ከሚበጣጠሱ
ቁርጥራጮች የሚሠራ ኣይደለም።
ከእዚህ በላይ ያለው ደብዳቤ በ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. የተጻፈልኝ በዓማርኛ የጽሕፈት መሣሪያ
ወይም ታይፕራይተር ነበር።
የደብዳቤውን ሥዕል ካቀርብኩበትም ምክንያቶች ኣንዱ ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ከማድረጌ በፊት የኢትዮጵያ የመንግሥት
መሥሪያ ቤቶች ይጠቀሙባቸው የነበሩት የኣማርኛ የመኪና መጻፊያ ፊደላት ምን እንደሚመስሉ ለማሳየት ነው።
ፊደላቱ ወረቀት ላይ የሚሠሩት ከሚቀጣጠሉ ቆብ፣ ጫማ፣ ቀለበትና ጭረት መቀጣጠያዎች
ነበር። ይህ የተደርገው የታይፕራይተር የመርገጫዎቹ ቁጥር ለሁሉም ፊደላት ስለማይበቃ በመሆኑ የታይፕ መጻፊያ
የተጠቀመው በዓማርኛ ፊደላት ኣይደለም። እነዚህንና የተመሳሰሉትን ቁርጥራጮች ከኣንድ የፊደል ገበታ መደብ
ከኮምፕዩተር እየቀጣጠሉ
ግዕዝ ነው የሚሉና ከዚህም ኣልፎ ለእነ ዩኒኮድ ያቀረቡና ሲያስቸግሩኝም የከረሙ ኣሁንም (፳፻፩)
ኣላረፉም።
እኔ
ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ያደረግኩት እዚህ በምታነቡት ፊደልና ለእያንዳንዱ ፊደል የተለየ የእራሱን ቦታ በመስጠት
ፊደላቱን ስምንት ፎንቶች ላይ በመበተን ሲሆን ይኸው ትክክለኛው የግዕዝ ፊደላችን
ኣሁን የዩኒኮድ
ፊደል ሆኗል።
የዓማርኛ የጽሕፈት መኪና ፊደልም ለብዙ
ሺህ ዓመታት በእጅና በብራና በኋላም በማተሚያ ቤት ሲጻፉ ከነበሩት ፊደሎቻችን በብዛትና ኣጠቃቀም ኣንድ ካለመሆኑም
ሌላ ተሻሽሎም የማያዋጣ ስለሚሆን ወደ ኮምፕዩተር እንዳይገባ ተቃውሜ ከጻፍኳቸው መካከል የ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. (1991
ኤ.ዲ.) ኢትዮጵያን ሪቪው መጽሔት እንግሊዝኛ ጽሑፌን
እዚህ ማንበብ
ይቻላል።
ዶ/ር ኣበራ
ሞላ
Updated 12/27/08 |