ዶክተር ኣበራ ሞላ

ቴክኖሎጂ

ግዕዝ በኮምፕዩተር

ኢትዮጵያ ለዓለም ካበረከተቻቸው የሚያኮሩ ቅርስዎችዋ የግዕዝ ፊደልዎችዋና የኣጻጻፍ ዘዴዎችዋ ኣንዱ ነው። በራሳችን ፊደላት፣ ኣኃዝና የጽሑፍ ምልክቶች ለብዙ ሺህ ዓመታት ስንጠቀም ቆይተናል። እንደጊዜው ሁኔታም በማሻሻል በማተሚያ መሣሪያዎችና በጽሕፈት መኪናዎች ለመጠቀም ችለናል።

ባለፉት ዓሥር ዓመታት የብዙ ኣገሮc የጽሑፍና የሥራ መሣሪያዎች ኮምፕዩተሮች ሆነዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊትም በእንግሊዝኛ የፊደል ገበታ ላይ የተመሠረተውን የጽሑፍ መኪና (Ethiopian Typewriter) የቅጥልጥል ኣጻጻፍ ዘዴ በኮምፕዩተር ለመጠቀም ተችሏል። የእንግሊዝኛን የፊደል ገበታ ወስዶ የግዕዝ ፊደላትን እንዲጽፍ ማድረግና ይኸንኑ ቴክኖሎጂ ወደ ኮምፕዩተር ማስተላለፍ የሚደነቅ ግሩም ሥራ ነው። የቅጥልጥሎቹ የጽሕፈት መኪና ፊደላት ኣጻጻፍ ከእጅ ጸሑፍ ቢያድነንም ያልተሟላ፣ ያልተስተካከለና ኣስቸጋሪ ከመሆኑም ሌላ የጥንቱም ሆኑ ዘመናዊው የእጅ ጽሕፈትና የማተሚያ ቤቶች ፊደሎቻችን የተቀጣጠሉ ኣይደሉም። ለምሳሌ 'ላ' በ'ለ' ቀኝ እግር ላይ በተቀጠለ ግንድ የሚሠራ ያልተለመደ ፊደል ሳይሆን እራሱን የቻለ ግራ እግሩ ያጠረ ፊደል ነው። ትክክለኛዎቹ የግዕዝ 'ለ' እና 'ላ' ፊደላት የቀኝ እግሮች ርዝመቶች እኩል ናቸው።

በቅርቡም ኢትዮጵያዊው ዶክተር ኣበራ ሞላ ለመጀመሪያ ጊዜ እያንዳንዱ የግዕዝ ፊደል ሳይቀጣጠል በኮምፕዩተር ሊጻፍና ሊታተም የሚቻልበትን breakthrough ዘዴ ለመፍጠር ችለዋል። በዚህም የተነሳ ከዚህ በፊት ሲደረግ እንደነበረው ፊደሎቻችን ለቴክኖሎጂው እንዲያመቹ ከመቀጣጠልና ከመቀናነስ ይልቅ ቴክኖሎጂው የፊደሎቻችንንና የእኛን ፍላጎቶች እንዲያሟላ ሆኗል። ኣዲሱ ዘዴ ቀልጣፋና ቀላል በመሆኑ እያንዳንዱ ፊደል የሚጻፈው ከሁለት መርገጫዎች ባልበለጡ ነው። ለምሳሌ ያህል ዊ ፊደልን ለመጻፍ የሚነኩት W እና F3 ወይንም W እና comma ወይንም W እና 3 ወይንም W እና I  !!! ወዘተ ናቸው። የሚታተመውም ፊደል እራሱን የቻለ ዊ እንጂ ዋ ላይ በሚቀጠል _  ወይንም ሰረዝ ኣይደለም። ይህ ኣዲስ ኣጠቃቀም የተለያዩ የኮምፕዩተር ቴክኖሎጂዎችን በኣቋራጭ ለግዕዝ ኣጻጻፍና ለኢትዮጵያ ኣሠራር ማውረስ እንድንችል ረድቷል። ይኸው የኮምፕዩተር ኅትመት ዘዴ ሞዴት (ModEth) በመባል በታወቀው የኢትዮጵያ ቃላት ማተሚያ (Publisher) ለኣይቢኤምና ተመሳሳይ ኮምፕዩተሮች ተዘጋጅቶ ብዙ ሰዎች በዓማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ኦሮምኛና ጉራጌኛ ፊደላት በመጠቀም ሥራ ላይ ኣውለውታል።

ይህ ጽሑፍ የተጻፈው በዚሁ ሶፍትዌር በሸዋ scalable ታይፕፌስ ዓሥር ፖይንት መደበኛ ፎንት ወይንም ሆህያት በHP Laserjet III ማተሚያ ነው። በበለጠ ለመረዳት የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌርን በስልክ ቁጥር (303) 972-2186 ማነጋገር ወይንም ለEthiopian Computers and Software, 9781 W. Fremont Pl., Littleton, Colorado 80123-4102, U.S.A. መጻፍ ይቻላል።w

ETHIOPIAN REVIEW / JANUARY 1991

© 1991 Ethiopian Review

ይህ ማርኛ ጽሑፍ በኅዳር ፲፱፻፹፫ ዓ!! ኢትዮጵያን ሪቪው መጽሔት ገጽ ፳ ታትሟል።

This Amharic article, on how Dr. Aberra Molla computerized Ethiopic was published in the Ethiopian Review magazine of January 1991.

.Last updated 6/28/2000


ኢትዮፒክ.ኮም
© ABSHA/ECS 1985-2000 1መብት2 የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር ፲፱፻፸፯-፲፱፻፺፪ ዓ!!