ከዶ/ ኣበራ ሞላ

ኤድስ

ኤድስ ወይም Acquired Immune Deficiency Syndrome (AIDS) በመባል የታወቀው በሽታ የሚመጣው ህዩመን ኢምዩኖደፊሸንሲ ቫይረስ Human Immunodeficiency Virus (HIV) በሚባል ጀርም ነው። በሽታው የሰውነትን የበሽታ መከላከያ በተለይ ነጭ ሴሎችን በማጥፋት ለቀላል በሽታዎች ለሕይወት ኣስጊ የመሆን ዕድል በመስጠት የሚገድል ነው። የሚተላለፈው ቫይረሱ ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ያልፀዳ መርፌ በመጠቀም ወይም ኣስፈላጊዎቹ ጥንቃቄዎች ሳይደረጉ በሚፈጸሙ የተለያዩ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች ነው። ኤድስን የሚያመጣው ሕይወት ያለው ጥገኛ ጠንቅ በኃይለኛ የማጉሊያ መሣሪያዎች ይታያል። ቫይረሱ ሰውነት ውስጥ እያለ እስከ ዓመታት የማይታመሙና በሽታውን የሚያስተላልፉ ጤነኛ ሰዎች ኣሉ።

የኤድስ በሽታ ሲጀምር ሰውነት ወይም ኣካላችን በቀላሉ የሚከላከላቸው ጀርሞች እንደፈለጋቸው በመባዛት ለሕይወት ኣደገኛ ሆነው ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል ጤነኛ መድን በነበረን ጊዜ ከማይተናኮሉን ባክቴሪያዎች ኣንዱ ኒሞንያ (Pneumonia) ያስከትላል። የቆዳ ካንሰር (Kaposi's Sarcoma) እና የኣንጎል በሽታም ሊኖሩ ይችላሉ። AIDS-related complex (ARC) ወይም ኣርክ የሚባሉ ምልክቶችም ሊመጡ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል የንፍፊት ማበጥ፣ የማይለቁ ትኩሳቶች፣ ድካምና ተቅማጥ፣ ክብደት መቀንስ (ከ፲ በ፻ በላይ) ደረቅ ሳልና ከባድ የእንቅልፍ ላብ ይገኙበታል። ትረሽ (Thrush) እና ሽንግልስ (Shingles) የሚባሉ በሽታዎችም ሊኖሩ ይችላሉ።

ኤድስ እንዳይዝ የምንከላከልበት የክትባት ዘዴ የለም። በሽታው ከያዘም በኋላ የሚፈውስ መድኃኒት የለም። በኣሁኑ ጊዜ ያለን መከላከያ በበሽታው እንዳንያዝ ኣስፈላጊዎቹን ጥንቃቄዎች ማድረግ ብቻ ነው። በሽታው እንዴት እንደሚተላለፍ በምርምር የተደገፉ መረጃዎችን በመከታተል ተረድቶ ቫይረሶቹ እንዳይሰራጩ ትክክለኛዎቹን ጥንቃቄዎች መከተልና ለሌሎችም ማስተማር የያንዳንዳችን ኃላፊነት መሆን ይገባል። ኤድስ ኣሰቃቂና ኣደገኛ በሽታ ቢሆንም እንደጉንፋን በቀላሉ የሚተላለፍ ስላልሆነ ልንከላከለው የምንችለው በሽታ ነው። ስለ በሽታው በሰፊው ማወቅ ባንፈልግ እንኳን በበሽታው እንዳንያዝ እንዴት እንደምንከላከል መረዳትና ወደ ሌሎች እንዳይተላለፍ እንዴት እንደምንጠነቀቅ ማወቅ እንደሚጠቅሙ ተረጋግጧል።

ኤድስ ቀስ በቀስ እየተስፋፋ የመጣው 1978 (፲፱፻፸ ..) ወዲህ ሲሆን እስከ 1985 ድረስ የተበከለ ደም በመወጋትና በመሳሰሉት ብዙ ሰዎች ያለቅብጠታቸው በበሽታው ተይዘዋል። 1988 ወዲህ ግን ኤድስ ሲይዝ ነጭ ሴል የሚሠራውን ኣንቲቦዲ (Antibody) በመመርመር የኤድስ ቫይረስ እንዳጋጠመን የሚጣራበት ፈጣን የምርመራ ዘዴ ስለተሠራ በተለይ የደም ማነስን ለመከላከል ሆስፒታል ከሚሰጠን ደም በመተላለፍ ሊይዝ የሚችለው ኤድስ ወደ መጣፋቱ ደርሷል።

ኤድስ በሚከተሉት ሁኔታዎች ሊተላለፍ ይችላል።

ከኤድስ በሽታ ለመከላከል የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይጠቅማል።

ቫይረሱ እንዳሌለበት ከማያውቁት (ወይም በሽታው ከያዘው) ሰው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ካስፈለገ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች መከተል ያስፈልጋል።

በተጨማሪም የሚከተሉት ታውቀዋል።

በሽታው በመካከላችን ስላለ ባለማወቅና በጥንቃቄ ጉድለት በኤድስ ብንያዝ ጥፋቱና ፀፀቱ የራሳችን ይመስለኛል። እስካሁን (1991) በዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ የኤድስ ቫይረስ ከተገኘባቸው ፪፻፸ሺህ ሰዎች መካከል ፩፻ሺህ (00, 000) በበሽታው ሞተዋል። በዓለም ላይም (፩፶፬ ኣገሮች) ኣንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤድስ በሽታ ተይዘዋል። (ሕዝቡም መጠንቀቅ ካልጀመረ በቫይረሱ የሚበከለው ሰው ቍጥር በየዓመቱ እጥፍ እየሆነ ሊቀጥል እንደሚችልና ለማስታመምም ብዙ ብሊዮን ዶላርስ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል።) ግብረ ሰዶም የሚያዘወትሩና ድረግ የሚወጉ ሰዎች በሽታ ነው እየተባለ ቸል ሲባል ቆይቶ ኣሁን የሁላችንም ጠር መሆኑ ስለተደሰረበት የሚፈለግብንን ብናከናውንና (ከመንግሥታትም ጋር) ብንተባበር በሽታውን መቆጣጠር (Control) ይቻል ይሆናል። የፈንጣጣን በሽታ ከዓለም ለማጥፋት (Eradication) ከጠቀሙን መካከል ክትባትና የሕዝቡ ትብብር ዋናዎቹ ናቸው። ስለ ግብረ ሥጋ ግንኙነት (Sexual) ማውራት ለማንኛውም ሕብረተሰብ ኣሳፋሪ ቢሆንም ኤድስ ያመጣብን ዱብ-ዕዳ የሕይወት ጉዳይ ስለሆነ መወያየት መጀመር ኣለብን።

ይህ ጽሑፍ የተጻፈው የሕክምና ዕርዳታ ለመስጠት ኣይደለም። በበለጠ ለመረዳት ሓኪሞቻችሁን ኣማክሩ። 1988 ለእያንዳንዱ የዩናይትድ እስቴትስ ቤተሰብ Understanding AIDS የተባለ ገጽ ጽሑፍ U.S. Department of Health ሲላክ ለእኔም እንደደረሰኝ ወደ ዓማርኛ ተርጕሜ ለሚፈልጉት መላክ እንዲቻል ጠይቄ በጀት ስላልመደበለት ያቀድኩት ኣልተሳካልኝም ነበር። የእዚህ መነሻ ይኸው HSS Publication No. (CDC) HHH 88-8404 ጽሑፍ ነው። ይኸንን የዓማርኛ ጽሑፍ ማንም እንደፈለገው ኣባዝቶ ማሰራጨት ይችላል።

ዶክ | ኤችቲኤምኤል | ፒዲኤፍ | ቴክስት

AIDS CLOCK

5/28/02
9/2/09

Copyright 1991 Ethiopian Review, ፲፱፻፹፫ ዓ.ም.

ይህ ጽሑፍ በኢዮፕያ ሪቪው መጽሔት ፌብርዋሪና ማርች ቅጾች፲፱፻፹፫ ዓ.ም. ነው።

This is a copy of an Amharic language paper on AIDS published by Dr. Aberra Molla in the March and April, 1991 G.C. issues of the Ethiopian Review monthly magazine.

Copyright 1985-2005 ABSHA/ECS

ኢትዮፒክ.ኮም | Ethiopic.com