
ዜናዊ መግለጫ
ሚያዝያ
፩፮
ቀን
፳፻፫
ዓ.ም.
ነፃው
ግዕዝኤዲት
ገጽ
በያሁ
እና
ቢንግ
በዓማርኛ
መፈለጊያ
ኣብሻ/ኢኮሶ ኩባንያ በዛሬው ቀን ኣዲስ የያሁ (Yahoo) እና ቢንግ (Bing) መፈለጊያ የግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ ኣቅርቧል። ይህም ግዕዝኤዲት ገጽ በዓማርኛ በነፃ የሚያስከትብ ኤችቲቲፒ://ፍሪታይፒንግ.ግዕዝኤዲት.ኮም ወይም http://freetyping.geezedit.com
በሚባል ድረገጽ ውስጥ ይገኛል።
ይኸንኑ መክተቢያ ሕዝቡ በነፃ እንዲጠቀምበት ኩባንያው ባላፈው ጥቅምት ድረገጹን በነፃ ማቅረቡ ይታወሳል። http://www.free-press-release.com/news-online-geezedit-for-typing-in-amharic-1266892997.html በእዚህ በተራቀቀ ኣዲስ ፈጠራ ግኝት ማንኛውንም የግዕዝ ፊደል፣ ኣኃዝ፣ ምልክትና ማዜሚያ ለመክተብ ከሁለት መርገጫዎች በላይ መጠቀም ኣያስፈልግም። ድረገጽ ላይ በነፃ የግዕዝኤዲት ገጽ ለመጠቀም በጣም ቀላል ሊሆን የቻለው የባለቤትነት መብቱ (ፓተንት / Patent) ከእዚህ በፊት ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ላደረጉት ኢትዮጵያዊ ዶ/ር ኣበራ ሊሰጥ እየተጠበቀ ባለበት በኣዲስና ሌላ ቴክኖሎጂ ላይ ስለተመረኰዘ ነው። ከድረገጽ ማንበብ የሚችል ማንም ተጠቃሚ በነፃ ከከተበ በኋላ ጽሑፉን ማረም፣ ማስቀመጥ፣ ማተምና ድረገጽም መሥራት የሚያስችል ውድና ኣዲስ ስጦታ ነው። ይህ ኣዲስ ግኝት ባይኖር የግዕዝ ተጠቃሚዎች ኣንዳንዶቹን ፊደላት ወይም ቅርጾች የሚከትቡት ከሦሶት እስከ ስድስት መርገጫዎች በመጠቀም ጊዜያቸውን በማባከንና ኣንዳንዶቹን ፊደላት ለመጻፍም ለግዕዝ ባዕድ በሆነው የእንግሊዝኛ እስፔሊንግ ዓይነት ለመክተብ እስከ ኣራት ፊደላትን ማየት ኣስፈልጓል።ዋየሎች ላይ ያሉትንና ኣንዳንዶቹንም ለመድገም ባዶ ስፍራን መጨመርና ድጋሚው ከተከተበ በኋላ ወደኋላ ተመልሶ ባዶውን ስፍራ ማጥፋትና ድጋሚውን በማውስ ወይም ቀስት መርገጫ መዝለል ኣስፈላጊም ነበር። ከዓማርኛ ሌላ የብዙዎቹ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ቋንቋዎች ፊደላት የበዙ ስለሆኑ የኣከታተባቸውም ኣሰልቺነት ለፊደሉ እድገት እንቅፋት ሊሆን ይችል ነበር።
ነፃው የግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ ግን በኣዲሱ የያሁ እና ቢንግ መፈለጊያ ለመጠቀም “Search” የሚለውን መጫን ኣንድ የመፈለጊያ ሳጥን ያወጣል። ከቀኝ በኩል ያለውን የተደፋ ቀስት መጫን ጉግል፣ ያሁ ወይም ቢንግ መፈለጊያን መምረጥ ያስችላል። ከሦስቱ ኣንዱን መርጦ መስመሩ ውስጥ በተለመደው የግዕዝኤዲት ኣከታተብ መጠቀም ዓማርኛውን በዩኒኮድ ፊደል መደብ ያስከትባል። ከእዚያም ከቀኝ የሚገኘውን “Search” መጫን ጉግል፣ ያሁ ወይም ቢንግ መፈለጊያ የሚያውቃቸውን የዓማርኛ ጽሑፎች ዝርዝር ያስቀርባል። የሚፈለገውን መርጦ መጫን ጽሑፉን ይከፍታል። ግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ በእንግሊዝኛ ለመፈለግ “Alphabet/ፊደል” ከእዚያም “Latin/ላቲን” የሚለውን መርጦ መጫን የሚፈለገውን ቃል ወይም ቃላት ሳጥኑ ውስጥ በእንግሊዝኛ የማስከተብና መፈለግ ምርጫ ይሰጣል።
ሰኔ ፪ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. ኣብሻ/ኢኮሶ ኩባንያ በነፃው የግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ በዓማርኛ ጉግል መፈለጊያ ኣቅርቦ ነበር። http://www.free-press-release.com/news-google-search-in-amharic-with-the-free-online-geezedit-1277218948.html
የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ በነፃው የግዕዝኤዲት ገጽ ውስጥ የያሁ እና ቢንግ መፈለጊያዎች ስለመጨ¿መራቸው ነው። ኣሁን ተጠቃሚው ከጉግል፣ ያሁ ወይም ቢንግ ኣንዱን መፈለጊያ መርጦ በዓማርኛ ፍለጋ እንዲጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ ስለቀረበ በጉግል ብቻ መተማመን ኣያስፈልግም።
የመላው ዓለም ድር ኣንድ ጥቅም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰነዶችና የመሳሰሉትን በፍለጋ ማግኘት ነው። የግዕዝ ኢንተርኔት ሰነዶችም ቍጥር እድገት መጨመር ቀጥሏል። ለምሳሌ ያህል ባለፈው የጎርጎርሳውያን ዓመት (2010) ነፃው የግዕዝኤዲት ገጽ ከ100,000 ጊዜ በላይ ታይቷል።
ለተጨማሪ መረጃ ግዕዝኤዲት.ኮም ወይም ኢትዮፒክ.ኮም ድረገጾች መጎብኘትና ኢ-ሜይልም ለኢትዮጵያዊው@ኤኦኤል.ኮም ወይም ግዕዝኤዲት@ኤኦኤል.ኮም መላክ ይቻላል። ኣድራሻው የኢትዮጵያ ኮምፕዩተሮችና ሶፍትዌር Ethiopian Computers & Software, 10145 E. 143 Way, Thornton, CO 80602, USA ኣሜሪካ ሲሆን የስልክ ቍጥሩ 1-303-835-8025 ነው።

Yahoo & Bing in Amharic in English በእንግሊዝኛ
5/14/2011
ከ፲፱፻፸፬ ዓ.ም. ጀምሮ ግዕዝ በኮምፕዩተር እንዲከተብ የፈጠረ!
©(መብት) ኣብሻ/ኢኮሳ ፲፱፻፸፯-፳፻፫ ዓ.ም.